ሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ

የመጨረሻ ደረጃ የደረሰ የዳሌ መገጣጠሚያ ችግር በዶ/ር ሳሜኤል የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ከተከናወነ በኋላ።

የዳሌ መገጣጠሚያ ኳስ የሚመስል ራስ እና ማቀፊያ ያለዉ መገጣጠሚያ ነዉ። የዳሌ መገጣጠሚያ ተቀባዩ ክፍል – የዳሌ ማቀፊያ(Acetabulum) በመባል የሚታወቅ ሲሆን ይሄዉም ለላይኛዉ የታፋ አጥንት ክፍል – የዳሌ ራስን (femoral head) እንደማቀፊያ ይይዘዋል። 

የዳሌ አጥንት በተለያዩ ምክንያቶች ማለትም፡- የመገጣጠሚያ ብግነት፣ ዳሌ ራስ መበስበስ፣ በስብራት ወይም በሌሎችምክንያቶች ጉዳት ሲደርስበት ቀላል የሚባሉ እና የዕለት ከለት ተግባራት የሆኑ እንደ መራመድ፣ መቀመጥ እና መነሳትእጅጉን አዳጋች እና በህመም የተሞሉ ሊሆኑ ይችላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የዳሌ መገጣጠሚያ በቂ እንቅስቃሴ ማድረግየማያስችል ከሆነ፤ ጎንበስ ብሎ ጫማ እንደማሰር ያሉ እንቅስቃሴዎችን ማድረግም ሆነ ተመቻችቶ መቀመጥም ከባድሊሆኑ ይችላሉ። 

መድሃኒቶችን መጠቀም፤ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴን ለዉጥ ማድረግ፤ እና የተለያዩ ድጋፎችን መጠቀም በበቂ ሁኔታህመምን የማያሽል ከሆነ የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ቀዶ ህከምናን ዘለቄታዊ መፍትሄ ይሆናል። የዳሌ ቅየራ ቀዶህክምና የህመም ስቃይን ለመቀነስ፣ በበቂ ሁኔታ እንቅስቃሴ ለማድረግ እና ወደ ዕለት ከለት ስራ ለመመለስ ዉጤታማእና ተመራጭ መፍትሄ ነዉ። 

የዳሌ ቅየራ ቀዶ ህክምና ማለት የዳሌ አጥንት መገጣጠሚያን በሰዉ ሰራሽ በሆነ የመገጣጠሚያ አካል (Prostheses) መተካት ማለት ነዉ። የዳሌ አጥንት መገጣጠሚያ ችግርን ከሚያስከትሉ መንስኤዎች መካከል በተለመደ መልኩበኢትዮጵያ ከምናስተውላቸው ችግሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ የመገጣጠሚያ ብግነት፣ የዳሌ ራስ መበስበስ፣ ከአደጋ ጋርተያይዞ የሚከሰቱ የዳሌ ስብራቶች እና ውልቃት፣ የተፈጥሮ የዳሌ መገጣጠሚያ ችግሮች፣ ቲቪ እና መሰል የዳሌመገጣጠሚያ እንፌክሽን ይገኙበታል። 

የዳሌ ቅየራ ቀዶ ህክምና እጅግ ዉጤታማ የሆነ ቀዶ ህክምና ቢሆንም ለሚቀየረው የሰዉ ሰራሽ አካል የአገልግሎትእድሜ ገደብ ስላለው የቅየራ ህክምናዉ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ እስኪታመንበት ድረስ ማዘግየቱ ይመከራል። የቀዶህክምናዉም ግብ የዳሌ ህመምን ለመቀነስ እና የማይወልቅ ሰው ሰራሽ ዳሌ መገጣጠሚያ በመቀየር አስፈላጊዉንየእለት ከለት እንቅስቃሴ ማድረግ ለማስቻል ነዉ። 

ቀዶ ህክምናዉም የተበላሸውን የዳሌ ራስ አጥንትን ቆርጦ ማውጣት እና የዳሌን ማቀፊያን ቅርፅን ማስተካከልይፈልጋል። በመቀጠልም የዳሌ ማቀፊያው ይተከል እና መቅኔ ውስጥ የሚገባ አካል ይደረጋል። ይኽም ለሚቀየረው የዳሌራስ ክፍል ድጋፍ በመሆን ያገለግላል።

ዶ/ር ሳሙኤል በትንሽ ጠባሳ፣ ጡንቻ ሳይቆረጥ፣ ከፊትለፊት በኩል የሚደረግ ሙሉ ዳሌ ቅየራ ቀዶ ህክምናንያከለናዉናል። 

አብዛኞቹ ታካሚዎቻችንም በቀዶ ህክምናዉ እለት ወደ ሆስፒታል በመግባት ከቀዶ ህክምናዉ በኋላ በሁለት ቀን ከሆስፒታል ይወጣሉ። አጠር ያለ የሆስፒታል ቆይታ እና ማገገሚያ ጊዜም በምናደርገዉ ጡንቻን በማይጎዳ እና ዘመናዊ ቴክኒኮችን በመተግበራችን እዉን ሆነዋል።

እያንዳንዱ ታካሚ የራሱ የሆነ ማገገሚያ ጊዜ ቢኖረዉም አብዛኞቹ ታካሚዎቻችን ግን ከ ሁለት እስከ 3 ወር ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ከቀዶ ህክምና በፊት ወደ ነበረዉ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ይመለሳሉ። በዚሁ መንገድ ከታከሙት ታካሚዎቻችን የአንዳቸዉን ምስክርነት በሚቀጥለዉ ቪድዮ ይመልከቱ።

የአርቲስት ፌቨን እናት ለልጃቸው የእሁድ ሰርግ ዝግጅት ላይ እንዳሉ ማክሰኞ ተሰብረው ሀሙስ ዶ/ር ሳሚ ጋ በጥቆማ መጥተዋል። ያጋጠማቸውን እና የሰርጉን ሁኔታ በምስለቅርፁ ይከታተሉ።

የዳሌ ቅየራ ህክምና እንዲደረግልዎ ካሰቡ ወይም በሃኪም ከታዘዙ ከ ዶ/ር ሳሙኤል ጋር ስለ አስፈላጊነቱ ወይም ሌሎች አማራጮች ቀጠሮ በመያዝ መማከር ይችላሉ። እያንዳንዱ ቀዶ ህክምና የራሱ የሆነ የሚያስከትለዉ ጉዳይ በመኖሩ የቀዶ ህክምናዉ አስፈላጊነት ላይ ጊዜ ወስደው ከሃኪምዎ ጋር መምከሩ የተሻለ ነዉ።

በ ሃምሌ 2013 ዓ.ም በዶ.ር ሳሙኤል ኃይሉ የተዘጋጀ እና የቀረበ

*ማስታወሻ:* በዚህ ጽሁፍ የተዘጋጀዉ መረጃ ለማስተማሪያነት የሚዉል ነዉ። ይሄም ጽሁፍ ሀኪም ማማከርን ሊተካ አይገባም። በዚህ ጽሁፍ ላይ ባገኙት መረጃ ምክንያት በኃኪምዎ የታዘዙትን ምክር ወደ ጎን መተዉ አይመከርም።