featured
የ 75 ዓመት አረጋዊት አዳልጧቸው በመውደቃቸው የቀኝ ዳሌ አንገት አጥንት ስብራት (Femur Neck fracture) ስለደረሰባቸው የቀኝ ዳሌያቸው በሚታየው መልኩ በተሰበረ ማግስት የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ብረት በፕላስቲክ፥ ጡንቻ ሳይቆረጥ ተደረጎላቸዋል።

ሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ | Total Hip Replacement

አገልግሎት ከምንሰጣቸው ውስብስብ የመገጣጠሚያ ቀዶ ህክምናዎች ውሰጥ መካከል አንዱ የሆነውን ሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራን (Total Hip Replacement) እናስተዎውቃችሁ።

ምንነቱ

ዳሌ መገጣጠሚያ በተለያዩ ምክንያቶች ስራው ሊስተጓጐል ይችላል። በዚህም ከአቅም በላይ የሆነ ህመም በማመጣት የቀን ተቀን ኑሮን ከባድ ያደርጋል። የተለያዩ ህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች፥ ፊዝዮቴራፒ እና መሰል ህክምናዎችንም መከታተል የመጀመሪያው የመፍትሄ ሂደት ነው። እነዚህን ተጠቅመን ህመሙ ለውጥ ካላገኘን እና የህመም ደረጃው ኑሯችንን በአግባቡ እንድንቀጥል ካላስቻለን፥ ሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ዘለቄታዊ መፍትሄ ነው።

ምክንያቶቹ

 • የዳሌ አንገት አጥንት ስብራት በእድሜ ጠና ያሉ እናት አባቶች ላይ ሲከሰት (Femur neck fracture in elderly)
 • የዳሌ ጭንቅላት መበስበስ (Avascular necrosis of femoral head/AVN)
 • የዳሌ አንጓ ብግነት (Hip Osteoarthritis)
 • የተለያዩ ዳሌ ላይ የሚያጋጥሙ ጉዳቶች እና ስብራቶች (Injuries)
 • ዳሌ ላይ የተከሰቱ እጢዎች (Tumors)
 • የዳሌ መገጣጠሚያ ነቀርሳ (Tuberculous hip arthritis) እና መሰል ችግሮቹ
 • ሩማቶይድ አርትራይቲስ (Rheumatoid arthritis) እና ሌሎችም

አይነቶቹ

 • ከ አጥነት ጋር በሲሚንቶ(cemented)፤ ወይም ሲሚንቶ በሌለው(cementless) የሚያያዝ ሊሆን ሲችል፥ ይኸም በሚከተሉት መልኩ ሊሰሩ ይችላሉ።
 • በተለመደው መልኩ የሚሰሩ፤ ማለትም
  • ከኋላ ወይም በጎን በኩል (traditional posterior or lateral approach)፤ ወይም
  • ዘመናዊ ጡንቻ ሳይቆረጥ፥ በትንሽ ጠባሳ፥ ከፊት በኩል በሚደረግ ቀዶ ጥገና (minimal invasive muscle sparing anterior approach) የሚሰራ ሊሆን ይችላል።
 • በማይካ (ceramic)፤ ወይም ብረት ከፕላስቲክ ላይ (metal on polyethylene) የሚሰራ ሊሆን ይችላል

ዳሌ መገጣጠሚያ ከማሰራታችን በፊት ማወቅ ከሚያስፈልጉን ነጥቦች በጥቂቱ

 • የቆዩ ተጓዳኝ ችግሮችን ማስተካከል (የስኳር፥ የልብ፥ ደም ግፊት፥ የጥርስ እና ሌሎች የጤና ችግሮችን በተለየ ሁኔታ ክትትል ማድረግ እና መታከም)።
 • መገጣጠሚያ ቅየራ ድንገተኛ ህክምና አይደለም (ለስብራት ከሚሰሩት ውጭ)፤ ስለሆነም የቀን ተቀን ኑሮን አዳጋች የሚያደርግ ህመም እስካላጋጠመ ድረስ ጊዜን ወስዶ መዘጋጀት ጥሩ ነው።
 • የሚሰራበት እቃ ብራንድ ለይቶ ማወቅ፤ የተቀየረው መገጣጠሚያ ረዘም ላለ ጊዜ እንዲኖር በተቻለ መጠን የሚታወቁ (አሜሪካ እና አውሮፓ ሰራሽ) መገጣጠሚያዎችን መጠቀም ረዘም ያለ የአገልግሎት ዘመን እንዲኖራቸው ያስችላል። 
 • ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ የአንድ ቀን ህክምና አይደለም። ስለሆነም ከሃኪምዎ ጋር ከቀዶ ጥገናው በፊት የዝግጅት ምክክር ማድረግ፤ ከተሰራ በኋላም ለተሳካ የማገገም ሂደት በባለሙያ የተደገፈ ፊዚዮቴራፒ እና እንቅስቃሴ መስራት ወሳኝ ናቸው። ከመሰራቱ በፊት እና ከተሰራም በኋላ ለቀሪ የእድሜ ዘመንዎ በሰራልዎት ሃኪም ክትትል ቢደረግልዎት የሚመከር ነው።

የዳሌ ቅየራ ህክምና እንዲደረግልዎ ካሰቡ ወይም በሃኪም ከተመከሩ ከ ዶ/ር ሳሙኤል ጋር ስለ አስፈላጊነቱ ወይም ሌሎች አማራጮች ቀጠሮ በመያዝ መማከር ይችላሉ። እያንዳንዱ ቀዶ ህክምና የራሱ የሆነ የሚያስከትለዉ ጉዳይ በመኖሩ የቀዶ ህክምናዉ አስፈላጊነት ላይ ጊዜ ወስደው ከሃኪምዎ ጋር መምከሩ የተሻለ ነዉ።

በ ነሐሴ 2013 ዓ.ም በዶ/ር ሳሙኤል ኃይሉ የተዘጋጀ እና የቀረበ

*ማስታወሻ:* በዚህ ጽሁፍ የተዘጋጀዉ መረጃ ለማስተማሪያነት የሚዉል ነዉ። ይሄም ጽሁፍ ሀኪም ማማከርን ሊተካ አይገባም። በዚህ ጽሁፍ ላይ ባገኙት መረጃ ምክንያት በኃኪምዎ የታዘዙትን ምክር ወደ ጎን መተዉ አይመከርም።

1 thought on “ሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ | Total Hip Replacement”

Leave a Comment

Send this to a friend