ልዩነታችን

ምቹ የታካሚ አገልግሎት፣ ቀጠሮ መያዣ እና መከታተያ ስርዓት።
በጥናት ላይ የተደገፈ የአጥንት ቀዶ ህክምና በመስኩ ተሸላሚ እና ልምድ ባካበቱ የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት፣ የመገጣጠሚያ ቅየራ እና ከፍተኛ አጥንት አደጋዎች ሰብ ስፔሻሊስት ያገኛሉ።

በተለየ ሁኔታ የምናተኩርባቸዉ የአጥንት ቀዶ ህክምና አገልግሎቶች፤

  • ጡንቻ ሳይቆረጥ የሚሰራ የሙሉ እና ግማሽ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ
    • በትንሽ ጠባሳ፣ ከፊት ለፊት በኩል የሚደረግ ዘመናዊ ዘዴ
  • የጉልበት ቅየራ
  • የዳሌ ገንዳ፣ ማቀፊያ እና ሌሎች ዉስብስብ ስብራቶች እና ውልቃቶች።

አገልግሎቶች

ሙሉ ዳሌ ቅየራ

በትንሽ ጠባሳ፥ ጡንቻን ሳይቆረጥ እና በ ዳሌ ፊት ለፊት በኩል በሚደረግ የዳሌ ቅየራ በሀገራችን ፈር ቀዳጅ እንደመሆናችን በልዩነት ቀዶ ህክምናዉን እናደርጋለን።

ሙሉ ጉልበት ቅየራ

አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እና በሀገረ አሜሪካ በሚመረቱ ሰዉ ሰራሽ የጉልበት መቀያየሪያዎችን በመጠቀም የጉልበት ቅየራ ህክምና እንሰጣለን።

ግማሽ ዳሌ ቅየራ

በፊት ለፊት በኩል በሚደረግ ቀዶ ህክምና ተደራራቢ ራስ ባለው አሜሪካ ሰራሽ መቀየሪያዎችን በመጠቀም የግማሽ ዳሌ ቅየራ ህክምና እናደርጋለን።

የዳሌ ራስ መበስበስ

የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ለሆኑ የዳሌ ራስ መበስበስ የዘረ ግንድ ህዎሳት ተከላ፤ ከ 3 እስከ 5ኛ ደረጃ ላሉ ደግሞ ጡንቻ ሳይቆረጥ በሚደረግ የዳሌ ቅየራ ቀዶ ህክምና እናደርጋለን።

የዳሌ ገንዳ ስብራት

ለዳሌ ገንዳ ስብራቶችን የቀዶ ጥገና የጉዳት መጠን ዝቅተኛ በሆኑ ዘዴዎች የሚከሰተዉን ደም መፍሰስ በመቀነስ እና ቀዶ ህክምናዉን በአጭር ጊዜ እንድናከናዉን ይረዱናል።

የዳሌ ማቀፊያ ስብራት

በሀገራችን ፈር ቀዳጅ የዳሌ ገንዳ እና ዳሌ ማቀፊያ አጥንት ስብራቶች ቀዶ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት እንደመሆናችን መጠን የነዚህን ስብራቶች ቀዶ ህክምና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እናከናውናል።

የዳሌ ስብራት

ለዳሌ አጥንት ስብራት እንደአስፈላጉነቱ በትንሽ ጠባሳ በሚደረጉ፣ የጉዳታቸዉ መጠናቸው አነሰተኛ በሆኑ እና ጡንቻ በማይጎዱ ዘዴዎች ህክምና እናደርጋለን።

ዉልቃት

ትኩስ ወይም ቆይተዉ ለሚመጡ የተለያዩ ዉልቃቶች በቀዶ ህክምናም ሆነ ያለ ቀዶ ህክምና የሚደረጉ ህክምና አገልግሎቶች እንሰጣለን።

ብዙ ቦታ የሚከሰቱ ዉስብስብ ስብራቶች

ለተለያዩ ዉስብስብ አጥንት ስብራቶችን ማለትም እንደ መገጣጠሚያ አካባቢ እና የተረከዝ ስብራቶች የጉዳት መጠናቸው አነስተኛ በሆኑ ዘዴዎች እናክማለን።