“እንደገና እናራምድዎታለን!”

ዶ/ር ሳሙኤል ኃይሉ

የአጥን ህክምና ስፔሻሊስበአዲስ አበባ

ዶ/ር ሳሙኤል የህክምና ዶክትሬት ድግሪ እና አጥንት ህክምና ስፔሻልቲ ጥናቱን በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ትምህርት ቤት ተከታትሏል። በመቀጠልም ከተለያዩ አለም አቀፍ ሆስፒታሎች ማለትም፤ ሲያትል በሚገኘዉ ሃርበር ቪዉ ህክምና ማዕከል፣ በኒዉ ዮርክ በሚገኘዉ የልዩ ቀዶ ህክምና ሆስፒታል እና ቺካጎ በሚገኘዉ ራሽ ፕረስበሪይቴሪያን ሆስፒታሎች የተለያዩ የቀዶ ህክምና ስልጠናዎችን ወስዷል። የሰብ ስፔሻልቲ ጥናቱንም በ ከፍተኛ አጥንት አደጋዎች እና መገጣጠሚያ ቅየራ በ ሳኒብሩክ ጤና ሳይንስ፣ በሆላንድ የአጥንት ቀዶ ህክምና እና መገጣጠሚያ ማዕከል፥ በቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ፥ ካናዳ ተከታትሏል።


ወደ ሀገር ቤት ከተመለሰም በኋላ በ አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ስፔሺያላይዝድ ሆስፒታል ከፍተኛ የዳሌ ገንዳ እና ዳሌ ማቀፊያ ስብራቶች ቀዶ ህክምናን በሰፊዉ አስጀምሯል። ሌላኛዉም ሰብ ስፔሻሊቲ ጥናቱም በሙሉ ዳሌ እና ጉልበት መገጣጠሚያዎች ቅየራ ነዉ። በምስራቅ አፍሪካም በትንሽ ጠባሳ እና ጡንቻን ሳይቆረጥ የሚደረገዉን የዳሌ ቅየራ ቀዶ ህክምና በማስጀመር ፈር ቀዳጅም ነዉ።

ከቤልጂየም ተጨማሪ ስልጠና በኋላ በኢትዮጵያ ዉጤታማ የሆነ ከፊትለፊት በኩል የሚደረግ ዳሌ ቅየራ ጽንሰ ሀሳብን በሰፊዉ አስተዋውቋል። ይሄም የህክምና ቴክሎጂ ፈረጀ ብዙ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን፤ ከነሱም መካከል፡- ቀዶ ህክምናን ተከትለዉ ከሚመጡ የጎንዮሽ ጉዳቶችን መቀነስ፣ መጠኑ ያነሰ ጠባሳ፣ ዉጤታማ የሆነ የቀዶ ህክምና ቴክኒክ እና የታካሚዉ አጠር ያለ ማገገሚያ ጊዜ ይገኙበታል።

በአሁን ሰዓትም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፥ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የከፍተኛ አጥንት አደጋዎች ቀዶ ህክምና ንኡስ ትምህርት ክፍል ኋላፊ በመሆን ያገለግላል። በትርፍ ሰዓቱም በሳማሪታን ቀዶ ህክምና ማዕከል ለህብረተሰቡ አግልግሎት በመስጠት ላይም ይገኛል።

በተለየ መልኩ ከሚያተኩርባቸዉ የአጥንት ቀዶ ህክምናዎች መካከል፡-

  • የዳሌ ቅየራ:
    • ከፊት ለፊት በኩል የሚደረግ እና ጡንቻ ሳይቆረጥ የሚሰራ ሙሉ እና ግማሽ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ (ሄሚአርትሮፕላስቲ)
  • ጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ
  • የዳሌ ገንዳ፥ ማቀፊያ እና ሎሎች የዳሌ አካባቢ ስብራቶች ቀዶ ህክምና
  • ዉስብስብ የአጥንት ስብራቶች እና ውልቃቶች ህክምና ይገኙበታል