Home

ስለ ዶ/ር ሳሙኤል

ዶ/ር ሳሙኤል በአዲስ አበባ የሚኖር የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሲሆን፤ በዳሌ እና ጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ እንዲሁም ከፍተኛ አጥንት አደጋዎች ሰብ-ስፔሻሊስት ነዉ። የተለያዩ የቀዶ ህክምና ስልጠናዎችን በሀገር ዉጪ ማለትም ሲያትል በሚገኘዉ ሃርበር ቪዉ ህክምና ማዕከል፣ በኒዉ ዮርክ በሚገኘዉ የልዩ ቀዶ ህክምና ሆስፒታል እና ቺካጎ በሚገኘዉ ራሽ ፕረስባይቴሪያን ሆስፒታሎች ተከታትሏል። ከዚያም የሰብ-ስፔሻሊቲ ጥናቱን በካናዳ በሚገኘዉ የቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ ጨርሷል። ከቤልጂዬም ሀገርም በትንሽ ጠባሳ ጡንቻ ሳይቆረጥ ስለሚሰራው ዘመናዊ የዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ተጨማሪ ስልጠናዎችን አግኝቷል። ዶ/ር ሳሙኤል ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚከናወኑ መገጣጠሚያ ቅየራዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ቅየራ ያከናወነ ሲሆን ልዩ ትኩረት ሰጦም ከፊት ለፊት በኩል የሚደረግ የዳች መገጣጠሚያ ቅየራ፣ የጉልበት ቅየራ እና ውስብስብ ስብራት ህክምናን ያከናውናል።

የቅርብ ጊዜ ጦማሮች

የታካሚዎቻችን ምልከታ

EXCELLENT
92 reviews on
Azeb Belete
2023-09-25
My dad could not walk and stop working due to his knee pain but after the operation my dad had a total knee replacement before 3 months, now he walks very well. Thanks to Dr. Samuel Hailu and his team professionalism, skill and ethics.
Samrawit Kassa Migora
2023-08-25
My dad's full hip replacement Surgey was performed by Dr. Samuel, who did an absolutely outstanding job.His hospital is excellent. Everything about my dad's surgery the personnel, the procedure, the technology, and the outcomes was perfect. He is incredibly professional and wonderful. We were astonished by how simple the pre- and postoperative periods were. We have complete faith in the medical staff at Samaritan Surgical Centre and heartily endorse Dr. Samuel and his staffs.
Addis Alemayehu
2023-06-03
My mom was having a bilateral hip replacement meaning both her pelvis are replaced,it was so good nowadays she has a gradual change we want a thank D.R Samuel Hailu!!!
Kidist Hailemariam
2023-04-23
Dr Samuel is a great doctor who helped my mother out so much.He was very polite and I’m grateful we have an amazing surgeon in Ethiopia.
eska keb
2023-03-31
ልክ አንድ ዓመት ሆነኝ በጤና ዕክል ምክንያት ሁለቱም እግሮቼ ላይ ከፍተኛ ህመም ተከስቶ ኦፕራሲዮን ካድረኩ:: ሁሌም የሚጠብቀን የእግዚአብሔርን ምህረት እና ቸርነት በዓይኔ አይቼ እንዳጣጥመው ዳግም በህይወቴ ያለፈች ውብ ቀን ይገርማል: የእግዚአብሔር ጥበብ ለሠው ልጅ የሰጠውን ረቂቅ ዕውቀትና ሥራ ቆሜ ሳስታውሰው ደነቀኝ የሐኪሜ የዶ/ር ሣሚ ማስተዋልና ታካሚን አንብቦ መረዳት አጃይብ ከሚያሰኝ የሕክምና ተሠጥዖ ጋር ያውም የሠውን አካል በልቶ ደም ሥርን ከጡንቻ: ጡንቻን ከአጥንት: አጥንትን ከደም አስተሣስሮ ወደ ነበረበት መልሶ ማስተካከል ወይ ጉድ እውነትም ቀዶ ጥገና። ከዶክተር ጋር አብረውት ተጀምሮ አስኪያልቅ ቀዶ ጥገናው ላይ የተሣተፋ የሕክምና አባላት ትህትናን ከብቃት ጋር ይዘው የተሯሯጡት አንደየሞያቸው ተፍ ተፍ ሲሉ እያየሁ አየሠማኋቸው ለአንድ ውጤት ያውም መራመድ ለተሣነው ህመምተኛቸው ጤናው ተመልሶ ዳግም አንዲራመድ ለሚደረግ ሩጫ ሲተጉ በዓይኔ ሣይ ነፍስያዬ አከበረቻቸው። ሆስፒታሉን ከክትትል ጀምሮ እስከ ኦፕሬሽን ብሎም እስከዚህ ጊዜ በረገጥኩ በሄድኩ ቁጥር ከንጽሕና እስከ ተቀናጀ የሕክምና መረጃ ሥርዓት ብሎም የጊዜን ዋጋ በአፈፃፀም በተግባር እስከሚከውን ሠውን ለመርዳት ንቁ እስከሆኑ ሠራተኞች ቤቱን ለታካሚ የሚመች ያደርገዋል። ህመሜ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠማኝ ከኦኘሬሽኑ ከአሥር ወር በፊት የተለመደውን የኤሮቢክስ ስፖርት እየሠራሁ ግራ እግሬን ከታፋዬ በላይ ከወገቤ በታች ባለው ክፍል ላይ ነበረ :በወቅቱ ረጃጅም የእግር የተራራ ጉዞ ከማድረጌ ጋር የተፈጠረ ጫና እና ከዕለቱ የስፖርት እንቅስቃሴ ጋር በማያያዝ ነበር ያሠብኩት: በዚህ ሁኔት የቆየው ህመሜ ገፅታውን ለውጦ ሁለተኛውንም የቀኝ እግሬን በመጨመር ጉዳዩ ከባድ መሆኑን ማስጠንቀቂያ ሰጠኝ። በጊዜው ከፍልውኃ እስከ እስፖርት ማሣጅ ወጌሻ ባለሞያ ብሞክርም የህመሙ መጠን እየጨመረ መራመድ እጅግ ስቃይ የተሞላው ወደ መሆን ተሸጋገረ ከነርቨ እስከ ወገብ ዲስክ በመታየት ጥልቅ ወደሆነ የሕክምና ምርመራ መነሻውንና ምንነቱን ለመለየት ብዙ ለፋሁ። በጸበል በእምነት እየታሸሁ ችግሩን በመጨረሻ ባዩኝ የሁሉ እሸት የህክምና ባለሞያ በተለየው መሠረት መፍትሔው ዘመኑ ከደረሠበት የሕክምና ደረጃ አንፃር በአገር ውስጥ እጅግ ውስን ቦታ ቀዶ ጥገናው እንደሚደረግ ካልሆነም በውጭ አገር ያለውን አማራጭ ያም ባይሆን ከህመሙ ጋር ተስማምቶ የት ድረስ መኖር እንደሚቻል መጨረሻውም ምን እንደሆነ ተረዳሁ ።በተጨማሪም በዘመኑ የመረጃ ቋት አነበብኩ። ችግሩን ማወቅ የመፍትሔው ግማሽ መንገድ ይሉት አባባልን በተግባር ተቀብዬ ፊቴን ወደ መፍትሔው አዞርኩ ከአገራዊ እስከ ውጭ ከባድ ነበር። በአንድ በኩል ህመሙ ከጤና መጓደሉ ጋር የሞራል ፈተና በሌላ በኩል የሕክምና አማራጩ ከአቅም ጋራ: ከዛ በዘለለ ከዕለት ኑሮ ትግል ጋር ከፍሲል ደግሞ ነገስ ህይወት በእንዴት ያለ ሁኔታ ይቀጥል ይሆን ከራስ ጋር ግብግብ እናም መፍትሔውን እራስንም ህመሙንም ተቀብሎ ፊት ለፊት መጋፈጥ የግድ ነበረ። በዝርዝር በተረዳሁት መሠረት የማይረሳኝ የማይተወኝ ፈጣሪዬን አስቀድሜ ከአቅምም ካለው አማራጮች በአገር ውስጥም በውጭም በመፃፃፍ አንድ እውነት ላይ ደረስኩ እግዚአብሔርም ረድቶኝ እጅግ በዘርፋ በዓለምዓቀፍ ደረጃ ምስጉን እና በሞያቸው ክቡር በሆኑት ድንቅ ወጣት ትሁት ኢትዮጵያዊ ሐኪም እጅ የመገጣጠሚያ አካል ቀዶ ጥገናዬን ለማድረግ ወሰንኩ። እሳቸውም እንደሐኪም ብቻ ሣይሆን እንደ ጓደኛ አንደ ጓደኛ ብቻ ሣይሆን አንደቅርብ ቤተሠብ አማካሪ ጥንቁቅ ነገርን ማቅለል የተካኑ ናቸው አና ለውሣኔ አልከበደኝም ። ልክ ይህን ማስታወሻ በምጽፍበት አንደኛ አመቴ በዚህች ሠዓት9:50 እምስት ሠዓት የፈጀውን የመገጣጠሚያ የሁለቱንም እግሮቼን ቀዶ ጥገና/bilateral hip joint replacement surger /በተሣካ ሁኔታ መጨረሳቸውን ፈገግ ብለው እያዩኝ ሲያበስሩኝ በግርምት ነበር እያየኋቸው congra ያልኳቸው። የእግዚአብሔር ሥራ ግርም ይላል ሕክምናው በዓለም እጅግ ከባድ በዛው መጠንም ውጤታማ ከሚባሉ የቀዶ ጥገና ቢሆንም በጣት የሚቆጠሩ የአገራችን ውጤታማ ባለሞያዎች አንዱና ዋነኛው ነዎትና ዶ/ር ሣሙኤል እንኳን ደስ አልዎ በባለፈው አንድ ዓመት ቀጥ ብዬ እራመዳለሁ እሮጣለሁ እቆማለሁ። ለኢትዮጵያም ለዓለምም እርሶን የሠጠን ፈጣሪ ስሙ ይመስገን የበለጠ ህዝብዎን የሚያገለግሉበት ዕድሜውን ጤናውን ዕውቀቱንና ጥበቡን አብዝቶ ይስጥልን :እርሶን መሠል የሞያ ልጆች ለብዙሃኑ እንዲሆኑ ቀርፀው እንደሚያወጡ እምነቴ ነው: ከሁሉ ከሁሉ በየትኛውም ሠዓት ለማማከር ለህመም በአካልም በስልክም በሶሻል ሚዲያም የሚገኙበት ዝግጅትዎ ለብዙዎች የሞያ ፍቅር ብቻ ሣይሆን የልብ ቅንነትዎ አርአያ የሚሆን ነውና አመሠገንኮት ከልብ ከሆነ ምስጋና እና አክብሮት ጋር ታካሚዎ እስክንድር ከበደ ❤❤❤፨ I would like to express my gratutude & heartful appreciation for Dr. Sammi and all the teams because just a year my health related to both legs become solved.  I have been done bilateral total joint hip surgery at  Samaritan Surgery Center . Right now at this time last year the operation was successfully completed , on the same talking i am now fully recovered and become healthy to do walking , running ,sitting and standing here and there Thank God for his blessing orthobedic wisdom of Dr.Sammi . He is a man of  solution , he is so kind  young professional to smooth matters to there end. His friendly approach and smart handling give me more comfort and confidence to think proud and lucky to do operation here in my country near to family and friends. So God Bless you Dr.
Eyob Kahisu
2023-03-18
Dr. Samuel is the most energetic and positive surgion i have ever had the privilage to be treated by. I thank him the most for my surgery that actually put back my arms back to where they were. No word would express my gratitude. Thanks Doctor for everything.
Zemam Befekadu
2023-03-11
Dr Samuel is very professional, humble and takes good care of his patients.
Daniel Abdissa
2023-03-01
We really appreciated the doctors' devotion to provide quality servive to us.
Asma Maxamed
2023-02-25
Waxan kalakulmay shaqo wanaag dhakhaatiir fiican kalkaalisooyin aad ufiican gabi ahaanba dhakhrkaa dhakh lamida.maan arag my dr samuel hailu nice dr

ለማናገር

የአጥንት ቀዶ ህክምናን ስለሚመለከቱ ጥያቄዎች ያናግሩን።

ለትኩስ ስብራት ድንገተኛ አገልግሎት በማንኛውም ሰዓት (24/7) ያለቀጠሮ ወደ ሳማሪታን ቀዶ ህክምና ማዕከል በመምጣት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።

ድንገተኛ ላልሆኑ ችግሮች ለመታየት ቀጠሮ በድረ ገጻችን ግርጌ ወይም ራስጌ በሚገኘው “ቀጠሮ ለመያዝ” የሚለውን በመጫን ከሚከፈተዉ ገጽ ላይ መጠይቆችን በመሙላት ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ።

ለማብራሪያ ሊያናግሩን በቴሌግራም፥ በስልክ ወይም በኢሜል ሊያገኙን ይችላሉ።

አድራሻ 1) ሳማሪታን የቀዶ ህክምና ማዕከል

ወሰን ሰንሻይን ሪል ስቴት ቤቶች የጀርባ በር፤ አሜሪካን ህክምና ማእከል አጠገብ።
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ቴሌግራም፡ t.me/DrSamuelHailu

ስልክ: +251-9 33 91 92 99

ኢሜል፡ info@drsamuelhailu.com

የጎግል ካርታ አድራሻችን

አድራሻ 2) መቅረዝ አጠቃላይ ሆስፒታል

ካዛንቺስ ከእናት ታወር ፊት ለፊት የቀድሞው ዮርዳኖስ ሆቴል

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ