“እንደገና እናራምድዎታለን!”

ዶ/ር ሳሙኤል ኃይሉ

ዶ/ር ሳሙኤል ኃይሉ፣ በአዲስ አበባ የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት

ዶ/ር ሳሙኤል የህክምና ዶክትሬት ድግሪውን በ2001 ዓ.ም እና የአጥንት ህክምና ስፔሻሊቲ ጥናቱን በ2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ትምህርት ቤት አጠናቋል፤ ከ2001 ዓ.ም ጀምሮም በዩኒቨርሲቲው በመምህርነት አገልግሏል። በመቀጠልም ከተለያዩ አለም አቀፍ ሆስፒታሎች ማለትም፤ ሲያትል በሚገኘዉ ሃርበር ቪዉ ህክምና ማዕከል፣ በኒዉ ዮርክ በሚገኘዉ የልዩ ቀዶ ህክምና ሆስፒታል እና ቺካጎ በሚገኘዉ ራሽ ፕረስበሪይቴሪያን ሆስፒታሎች የተለያዩ የቀዶ ህክምና ስልጠናዎችን ወስዷል። የሰብ ስፔሻልቲ ጥናቱንም በ ከፍተኛ አጥንት አደጋዎች እና መገጣጠሚያ ቅየራ በ ሳኒብሩክ ጤና ሳይንስ፣ በሆላንድ የአጥንት ቀዶ ህክምና እና መገጣጠሚያ ማዕከል፥ በቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ፥ ካናዳ ተከታትሏል።


ወደ ሀገር ቤት ከተመለሰም በኋላ በ አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ስፔሺያላይዝድ ሆስፒታል ከፍተኛ የዳሌ ገንዳ እና ዳሌ ማቀፊያ ስብራቶች ቀዶ ህክምና ላይ ትኩረት አድርጓል። ሌላኛዉም ሰብ ስፔሻሊቲ ጥናቱም በሙሉ ዳሌ እና ጉልበት መገጣጠሚያዎች ቅየራ ነዉ። በትንሽ ጠባሳ እና ጡንቻን ሳይቆረጥ የሚደረገዉን የዳሌ ቅየራ ቀዶ ህክምና ይሰራል።

በቤልጂየም ከፊት ለፊት በኩል በሚደረግ የዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ላይ ተጨማሪ ስልጠና ወስዷል። ሊገኙ ከሚችሉ ጥቅሞች መካከል አነስተኛ ጠባሳ እና አጭር የማገገሚያ ጊዜ ይገኙበታል፤ ጥቅሞቹ እና ስጋቶቹ ከእያንዳንዱ ታካሚ ጋር በምክክር ወቅት ይታያሉ።

ዶ/ር ሳሙኤል ኃይሉ የአጥንት ህክምና ተባባሪ ፕሮፌሰር፣ የአዲስ ኦርቶ (ፈቃድ ያለው የአጥንት ህክምና መሳሪያዎች አቅራቢ፤ የህክምና አገልግሎት አይሰጥም) መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ እንዲሁም ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በሳማሪታን ቀዶ ህክምና ማዕከል የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ነዉ።

ከፌሎውሺፕ ስልጠናው በፊትም ሆነ በኋላ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሰርቷል። ከ2008 እስከ መስከረም 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፥ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የከፍተኛ አጥንት አደጋዎች ንኡስ-ክፍልን በኋላፊነት መርቷል፤ በዚህም የአጥንት ከፍተኛ አደጋዎች ሰብ-ስፔሻሊቲ ፌሎውሺፕ ስልጠና አቋቁሞ ለአምስት ዓመታት በፕሮግራም ዳይሬክተርነት መርቷል። ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍለ ሃገራት እንዲሁም ከናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ማላዊ እና ኬንያ የመጡ ፌሎዎችንም አስተምሯል።

ዶ/ር ሳሙኤል በዓለም አቀፍ ደረጃ በተጋባዥ መምህርነት ያስተምራል። ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በሪችላንድ፣ ዋሽንግተን በሚካሄደው የSIGN Fracture Care International ዓመታዊ ጉባኤ ላይ የዳሌ ገንዳ ቀዶ ህክምና ወርክሾፖች መምህር ሆኖ አገልግሏል። በAO Alliance ሀገር አቀፍ እና አህጉራዊ የስብራት ህክምና ኮርሶች ላይ በመምህርነት እና በሰብሳቢነት ያገለግላል፤ የAO Alliance የኢትዮጵያ ኢኒሼቲቭ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልም ነው። ለስድስት ዓመታት የኢትዮጵያ የአጥንት ህክምና እና ትራውማቶሎጂ ማህበር (ESOT) ዋና ጸሐፊ በመሆን አገልግሏል። በጥቅምት 2014 ዓ.ም የOrthopaedic Trauma Association (OTA) ዓመታዊ ስብሰባ ላይ የ2020 OTA Humanitarian Scholar በመሆን እውቅና ያገኘ ሲሆን፣ በመጋቢት 2009 ዓ.ም ደግሞ በኢትዮጵያ የዳሌ ገንዳ እና ዳሌ ማቀፊያ ቀዶ ህክምና ላበረከተው አስተዋጽኦ ከኢትዮጵያ የአጥንት ህክምና እና ትራውማቶሎጂ ማህበር (ESOT) ከፍተኛውን የክብር ሽልማት (Highest Merit Award) ተቀብሏል። በተጨማሪም የOTA ዓለም አቀፍ የምርምር ድጋፍ (International Research Grant) እና የESOT የምርጥ ሳይንሳዊ ጥናት ሽልማት ተቀብሏል። በጥቅምት 2018 ዓ.ም በሃርቫርድ ሕክምና ትምህርት ቤት የማስተማሪያ ሆስፒታል በሆነው Beth Israel Deaconess Medical Center በተዘጋጀው 21ኛው Augustus A. White III ሲምፖዚየም ላይ የግራንድ ራውንድስ ትምህርት እና ዋና ንግግር (keynote) አቅርቧል።

በተለየ መልኩ ከሚያተኩርባቸዉ የአጥንት ቀዶ ህክምናዎች መካከል፡-

  • የዳሌ ቅየራ:
    • ከፊት ለፊት በኩል የሚደረግ እና ጡንቻ ሳይቆረጥ የሚሰራ ሙሉ እና ግማሽ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ (ሄሚአርትሮፕላስቲ)
  • ጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ
  • የዳሌ ገንዳ፥ ማቀፊያ እና ሎሎች የዳሌ አካባቢ ስብራቶች ቀዶ ህክምና
  • ዉስብስብ የአጥንት ስብራቶች እና ውልቃቶች ህክምና ይገኙበታል

ምርምር እና የታተሙ ጥናታዊ ጽሁፎች

በዓለም አቀፍ እና በሀገር ውስጥ መጽሔቶች ላይ ከታተሙ ጥናታዊ ጽሁፎች መካከል (በእንግሊዝኛ)፦

  • Kadiyala S, Almeida CG, Mengesha MG, Adem EG, Berwin J, Ali AS, Hailu S, Agarwal-Harding KJ. Assessing barriers to musculoskeletal trauma care in Ethiopia: a national providers’ survey. BMC Health Services Research, 2026. ያንብቡ
  • Melkamu S, Alemayehu G, Hailu S. Radiographic assessment of pelvic inlet and outlet view angles in the Ethiopian population. JBJS Open Access, 2024;9(3):e24.00015. ያንብቡ
  • Armstrong E, Rogers K, Li CS, et al., including Hailu S; INORMUS Investigators. Time from injury to hip-fracture surgery in low-income and middle-income regions (INORMUS). The Lancet Healthy Longevity, 2024;5(8):e552–e562. ያንብቡ
  • Bimer GA, Wamisho BL, Hailu S, Alemayehu G. Patient self-reported functional outcomes after total hip arthroplasty: insights from a tertiary hospital in Ethiopia. Ethiopian Medical Journal, 2024;62(Suppl 1). ያንብቡ
  • Tena T, Mengesha MG, Alemayehu G, Hailu S. Determinants of early complications in femur neck fractures following operative management in a resource-limited setting. Ethiopian Medical Journal, 2024;62(Suppl 1). ያንብቡ
  • Ogunlusi JD, Yusuf MB, Hailu S, et al. Knowledge and practice of pelvic and acetabular fracture management among orthopaedic and trauma surgeons in Nigeria. Sierra Leone Journal of Medicine, 2024;1(1):10–15. ያንብቡ
  • Hailu S, Tesfaye S, Alemayehu G. Osteoporosis-related appendicular fractures in Tikur Anbessa Specialized Hospital, Ethiopia: a prospective observational study. Archives of Osteoporosis, 2023;18:21. ያንብቡ
  • Hailu S, Leulseged A, Lemma S. Patient-reported outcome measures for acetabular fractures treated operatively without a C-arm in Ethiopia. Journal of Bone and Joint Surgery, 2022;104(23):2083–2094. ያንብቡ
  • Hailu S, Gebre H, Alemayehu G. Orthopaedic injury patterns at a tertiary referral hospital in Ethiopia: a prospective observational study. Injury, 2022;53(10):3195–3200. ያንብቡ